ታላቅነት የሚፀነሰው መፃህፍትን በማንበብ ውስጥ ነው!
የንባብ ትሩፋትከማንበብ የምናተርፈው እልቆ መሳፍርት ጥቅሞችን ነው፡፡ ከነዚህ አንዱ እውቀት ነው፡፡ በዕውቀት የተኖረ ሕይወት መገለጫ ደግሞ ሚዛናው አስተሳሰብና ምክንያታዊ ውሳኔ ሰጪነት ነው። ንባብ ውስጥ ልዩ ሕይወት አለ፤ ንባብ ውስጥ የምንፈልገውን ነገር ማግኘት አለ፤ ታላቅነት የሚፀነሰው መፃህፍትን በማንበብ ውስጥ ነው፣ ምን እንደምታነብ ለማሰብ ጊዜ ውሰድ፤ ካነበብከው ውስጥ የሚያስደስትህን የምታምንበትን ለማድረግ አንድ እርምጃ ጀምር ከዛ የምትፈልገው ነገር እስኪፈጠር ድረስ ጥረትህን አታቁም ፣ ማንበብ ከፍታህ ላይ የምትደርስበት ቀናው ጎዳናህ ነው፡፡ አራዳ ለመሆን ከፈለክ፣ ሁሉን አወቅ ለመሆን ካሰብክ፣ በአንድ ነፍስ ብዙ ለመኖር ከወሰንክ፣ አለማችንን በንስር አይን ለማየት ከቆረጥክ ወደድክም ጠላህ መፃህፍትን ማንበብ አለብህ፣ ያላነበበ ሁሉ ድብን ያለ ፋራ ነው። አይኑ የሩቁን አይደለም፣ የቅርቡንም አጥርቶ አያይም።«መልህቅ – ዘነበ ወላ
Responses