ብቸኛ መሸሸጊያዬ ናት
እሷ የህሊና ምግብ ሙዳይ ናት። ምንም ብሆን፤ ምንም ባጣ የማይደንቀኝ ልበ ደንዳና እንደሆንኩ ያለፍኩበት ጨለማ ይመሰክራል፤ እሷ ብቻ ከእኔ ጋ ትሁንልኝ እንጂ የትም ይመቸኛል። እሷን ያላገኘሁ ቀን ነው መንፈሴ የሚታወከው፤ እሷ ካለችበልቤ ሀሴት ሞልቶ እንደተመላለሰ የተሰፈረለኝን ዘመን ጨርሳለሁ።ላንለያይ ተዋደናል።
እሷ የልቤ ብርሃን ናት፡፡ ግፍን እቋቋም ዘንድ የተቸረችኝ ጫንቃዬ ናት፤ በንፅሕና ከእውነት ጋ እንድቆም፤ አቋሜ እንዳይሸረሸር፤ መንገዴንየምትመራኝ የሚስጥር ሙዳይ፣ በፍቅር ˚ ከመንገዴ እንዳልሰናከል በትልቁ አቅም ሆናኛለች፡፡
በጠላትና በአሰናካይ፣ተከብቤ እንዳላፈገፍግ የምታበረታኝ የደስታዬ ፍላጽ ብቸኛ መሸሸጊያዬ ናት። የዓላማዬን ያህል ነው የምወዳት……….መጽሀፌ ጓደኛዬና መምህሬ፣ መካሪዬና መዝናኛዬ፣ ሁሉነገሬ ናት። አንቺ ስላለሽኝ እኔ በኩራት እራመዳለሁ፣ ከእስትንፋሴ እኩል አብረሽኝ ትኖሪ ዘንድ ቃልኪዳን ገብቻለሁ።
Responses