ስታነብ ፥ የምታውቀው ህይወትን ነው።
ማንበብ አዕምሮን ይገነባል። በአዕምሮ ውስጥ ቋንቋን – የግንዛቤ(cognitive) እድገትን – ማህበራዊ እና emotional እድገትን . . . የሚያበረታቱ ግንኙነቶችን ይፈጥራል። ማንበብ መሠረትን ይገነባል። በምታምነው እንድትጠነክር – የምታምነውን ብዙ እያወከው እንድትሄድ ያደርጋል። ስታነብ ብዙ የምታውቀው እንዳለ እያሰብኽ ትሄዳለህ። አንባቢ ከሆንኽ ደግሞ የማታውቀውን ለማወቅ እየጣርኽ – ሁሉን እየፈተሽኽ ትመጣለህ። “እያወቅኽ ትሄዳለህ” ሲባል ግን የተለየ ነገር አይደለም ምታውቀው። የተለየ ፍልስፍና አይደለም ምታውቀው። ስታነብ ፥ የምታውቀው ህይወትን ነው። የምታውቀው የማታውቃቸውን ሌሎች ሰዎችን ፤የምታውቀው ሌሎች አዳዲስ ባህርያትን ነው። የምታውቀው ጥንካሬ ምን እንደሆነ – ፅናት ምን እንደሆነ -ማፍቀር ምን እንደሆነ – ሽንፈት ምን እንደሆነ – ጥላቻ ምን እንደሆነ – ራስ ወዳድነት ምን እንደሆነ . . . ነው ምታውቀው። የምታውቀው የማታውቀውን ነገር ነው። የምታውቀው ውስጥህ ተቀምጦ ያላስተዋልኸውን/ያላወቅኸውን ነው። አዋቂ ውስጡ ላይ ያለውን የሚያውቅ ነው። ማወቅ ደግሞ ወደ ውስጥ ያለውን ማስተዋል ነው። ማንበብ ደግሞ ውስጥ ላይ ያለውን ነገር ማወቂያ መንገድ ነው። አነባብን ማወቅ ደግሞ ትክክለኛለው መንገድ ነው።
Responses