ራስን ለማሻሻል የንባብ መንፈስ መያዝ
አንባቢ ሰዎች ካለማቋረጥ በመማር እና ራሳቸውን በማሻሻል የታወቁ ናቸው። ለመሻሻል ደግሞ የንባብን መንፈስ እንደያዙ መቆየት ግድ ነው።
የሚያነቡ ሰዎች በደረሱበት ደረጃ እና እውቀት በፍጹም አይኩራሩም፤ በምትኩ፣ ‘ከዚህ በኋላ መድረስ ያለብኝ ደረጃ ምንድን ነው? ምንስ ነገር ማወቅ አለብኝ?’ በሚሉት ጥያቄዎች የተሞሉ ናቸው።
ማንበብናእናመሻሻል ማቆም አንድ ሰው በራሱ ላይ ሊያደርስ ከሚችላቸው ከባድ በደሎች መካከል ዋነኛው ነው። ራስን በድሎ ሌሎችንም በእርሱ ተፅዕኖ ሥር ያሉትን ሁሉ ይበድላል። የእውቀት እና የመረጃ ለውጦች እረፍት በማይሰጡበት በዚህ ዘመን ወደ ፊት አለመራመድ ማለት ወደ ኋላ መቅረት ማለት ነው። አንድ ሰው ራሱን ካላሻሻለ ፈጠነም ዘገየ ከእርሱ በልጦ የተገኘ ሰው እንደሚተካው ሊያስታውስ ይገባል። ከዚህ ለውጥ ጋር ያልተራመደ ሰው ደግሞ የሚጠብቀው በነገሮች ሁሉ ወደ ኋላ መቅረት ነውና ላለመበለጥ እና ላለመቀደም ቀድሞ መገኘት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።”
Responses