ማንበብ በድንቁ*ርና ላይ ለማመጽ የሚደረግ እርምጃ ነው
ሕይወት የትናንት ፣ የዛሬ እና የነገ ድግግሞሽ ነው። እስካሁን የኖርነው ሕይወት በዚህ ድግግሞሽ ውስጥ ነው። ይኼን ድግግሞሽ ውጤታማ ለማድረግ እና ከአስልችነት ለመውጣት መጽሐፍ ወሳኝ ነገሮች ናቸው። በማንበብ ውስጥ ያልተቋረጠ ሕይወት መኖር ይቻላል። በልደት የተጀመረ ግን በሞት የማይቋረጥ፤ አድስ እና ልዩ አኗኗር። በመጽሐፍት ውስጥ ይኽ ዘለዓለማዊነት አለ። ስታነብ የዛሬን ብቻ ሳይሆን የትናንት እና የነገም ሕይወት ይኖርኻል። ይኽን ዑደት ለማስቀጠል ሦስት ነገር ማድረግ ዛሬ ማንበብ ፣ ማንበብ እና ማንበብ ብቻ። ያለፍነው ትናንት ዛሬ ነበር ፣ የምንኖረው ዛሬ ለነገ ቀድሞት የተገኘ ትናንቱ ነው።
ሁሌም ዛሬ እናንብብ ትናንት እና ነገን ለመኖር ይረዳል።
ይኽ በድንቁ*ርና ላይ ለማመጽ የሚደረግ እርምጃ ነው::!!!!!
Responses