ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም!!!!

መፃሕፍትን ከማንበብ ባሻገር በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከሃሳባችን ጋር በማስተያየትና በማሻሻል፣ በማሠላሠልና በማስተዋል አዲስ ሃሳብ ካልፈጠርንበት መፅሐፍ ማንበብ ሳይሆን መፅሐፍ መቁጠር ነው የሚሆነው፡፡ ባነበብነው ሃሳብ ተገዝተንና አዲስ የባህሪ ለውጥ ወይም አዲስ ነገር ካልፈጠርንበት ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ዕውቀት ስንል በተጨባጭ በተግባር የሚገለፅ ነውና፡፡ስለሆነም የምናነበውን ከህይወት ዘይቤያችን ጋር አሰናስለን ለተሰማራንበት ሙያ መሻሻልና ራሳችንንም ብቁ ለማድረግ በሚጠቅም መልኩ እናንብብ፣ ያኔ ልዩነት ፈጣሪዎች ሆነን ወደከፍታችን እንወጣለን፣ ስኬታችንን እናጣጥማለን። ኢዮብ ጽጌ ነሀሴ 21,2016

Related Articles

ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም

መፃሕፍትን ከማንበብ ባሻገር በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከሃሳባችን ጋር በማስተያየትና በማሻሻል፣ በማሠላሠልና በማስተዋል አዲስ ሃሳብ ካልፈጠርንበት መፅሐፍ ማንበብ ሳይሆን መፅሐፍ መቁጠር ነው የሚሆነው፡፡ ባነበብነው ሃሳብ ተገዝተንና…

ንባብ በአዲስ ሀሳብ ለመመራት!!!

የሰው ልጅ ምክንያታዊ፤ የሚጠይቅና የሚመራመር መሆኑየታመነ ነው፡፡ በዚህ አስተሳሰብ መሰረትም ህዝባችን ለሚገጥሙት ችግሮች ዘመኑን የዋጀ፣በዕውቀት ጎዳና የሚራመድ በማስተዋልና በሥርዓት የሚጓዝ  ትውልድ ማፍራት ይኖርበታል። ይህን ማግኘት…

ንባብ አሰላሳይ ያደርጋል

ንባብ ህሊናን አሰላሳይ ያደርጋል። የአንባቢ ኅሊና ጽልመተ ኅሊናን ታበራለች ቁረተ ልቡናን ታግላለች፡፡አለማወቅን ያህል ደዌን ትፈውሳለች፡፡አለማወቅን ያህል በሽታ ይዞ ሰው ጤነኛ ሊባል አይችልምና፡፡ አንባቢ ሰው የሐሳብ…

Responses