መጽሐፍት ጥሩ ወዳጆች ናቸው!
መጽሐፍት ጥሩ ወዳጆች ናቸው! ከዘመን ዘመን የማይለወጡ ታማኝ ወዳጆች። የያዙትን ጥበብ ያለስስት የሚያካፍሉ፣ ቁምነገር የሚያቀብሉ የህይወት ዘመን ባለውለታ ናቸው። “መጽሐፍት አዝናኝ እና አስተማሪ ናቸው፡፡ የሰዎችን ህይወት ይዳስሳሉ፣ ተደራሲውን በውስጣቸው አስገብተው ሰቅዘው በመያዝ በገጸ ባህሪያት ደስታና ሀዘን እያስደሰቱ፣ እያዝናኑና እያስተማሩ እንደ ጥሩ ወዳጅና ጓደኛ በተደራሲው አዕምሮ የማይረሳ ድንቅና አስተማሪ አሻራቸውን ጥለው ያልፋሉ፡፡” እኛም ባለፈው አመት በርካታ የንባብ ትሩፋቶችን ወደናንተ አድርሰን፣ የንባብን ባህል በማሳደግ በስብዕናችን፣ በአመለካከታችን፣ በስራችን፣ በንግግራችን፣ በአመራራችንና በሁለንተናዊ የህትወት ዘይቤያችን ተሽለን ለመገኘት በ2017 የመጽሀፍት ወዳጆች ትሆኑ ዘንድ መልዕክታችን ይድረሳችሁ።
Responses