ልብ ላለው ንባብ ለማወቅና ለመለወጥ ትልቅ ዕድል ነው።
ልብ ላለው ንባብ ለማወቅና ለመለወጥ ትልቅ ዕድል ነው።
ማንበብ፣ በብዙኀን መገናኛዎች ተረክ ፣ በትምህርት እና በአፈታሪክ በኩል የምናውቃትን ደብዛዛ ዓለም አጥርቶ በማሳየት አመለካከታችንን ያስተካክላል ፤ የአስተሳሰብ አድማሳችንን እያሰፋ የጠባብነት ቋጠሯችንን ያላላል፤ ከማይጨበጡ የቃላት ድርድሮች እና ከሙልጭልጭ የሐሳብ ውዥንብሮች አላቅቆ ከገሃዱ ዓለም እውነታ ጋር ያገናኛል።
… ማንበብ የሌሎችን እንድናደንቅ ዕድል ከመስጠቱም ባሻገር ራሳችንን በሌላ አንጻር እንድናይ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩ ባሻገር ንቀን ለተውነው ማንነታችን ወይም የማንነታችን መገለጫዎች ዋጋ እንድንሰጥ ይቆሰቁሰናል።
ይህ ራስን፣ማንነትን፣ አብሮን ያለውን ዙሪያችንን ለማወቅና ለመለወጥ የሚረዳንን ሀይል እንጎናፀፍ የዕለቱ መልዕክታችን ነው።
Responses