ለማንበብ ጊዜ ስጡ!!!!!
ለማንበብ ጊዜ ስጡ። ስታነቡ እያያችሁት የህይወታችሁ ዘይቤ ሲሻሻል፣ ለነገሮች ያላችሁ አረዳድና አመለካከት ሲቀየር ታዩታላችሁ፣ ከጥድፊያና ከስሜታዊ ውሳኔ ትርቃላችሁ፣ በማንበብ ከምታገኙት እውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ በመነሳት ለሚገጥማችሁ ፈተናና ችግር መፍትሄ መስጠት የሚያስችል አቅም ትጎናፀፋላችሁ። መቼ እሺ የቱን እምቢ ማለት እንዳለባችሁ በማወቅ ለፀፀት ከሚዳርግ ችኩል እርምጃ ራሳችሁን ትታደጋላችሁ።ስለሚለውጣችሁ፣ ስለሚያሻሽላችሁ፣ ስለሚያረጋጋችሁ፣ስለሚያሳውቃችሁና ስለሚጠቅማችሁ ለማንበብ ጊዜ ስጡ ። በየዕለቱ ራሳችሁን ገንቡ። የዛሬ መልዕክታችን ነው።
ኢዮብ ጽጌ
ጥቅምት 16
Responses