እንዳነብ የሚያደርገኝ ምንድነው?
እንዳነብ የሚያደርገኝ ምንድነው? ስንቶቻችን ይህንን ጥያቄ ለራሳችን ጠይቀን እናውቃለን? ወደ ንባብ የሚገፋፋኝ ሀይል የማወቅ ጉጉት ነው። አዲስ ነገር መናፈቅ፣ የተሰወረን ለመግለጥ መጓጓት፣ ታሪክን ለመመርመር፣ ትርክትን ለማረም፣ መረጀን ለመታጠቅ፣ እውነትን ለመረዳት መሻት ነው እንዳነብ የሚያደርገኝ ሀቅ።
እንዳነብ የሚገፋፋኝ፣ ትንሽ እውቀት ይዛኝ እንዳትጠፋ፣ ጥራዝ ነጠቅነት እንዳያስተዛዝበኝ፣ ጥልቅ መረዳት ስለሚያስፈልገኝ፣ በሰዎች ዘንድ ሀይል ስለሚሆነኝ ማንበብ እንደሚያሳርፈኝ ስለማምን ነው። እናንተም ይህንን ገፊ ሀይል ለመጎናጸፍ ካስፈለጋችሁ የማንበብ ፍላጎት በአንድ ቀን የሚመጣ ሳይሆን በብዙ ድግግሞሽና በትንሽ በትንሽ የሚደረግ የማያቋርጥ ትግል ውጤት መሆኑን ተረድታችሁ ፍሬ የሚያፈራ ንባብ በልምምዳቹ ይኑር እላለሁ።
ኢዮብ ጽጌ
ሐምሌ 13, 2016
Responses